አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ጋር በስልክ ተወያዩ።
ውይይቱን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ፥ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ጋር በስልክ መወያየታቸውን አስታውቅዋል።
“በነበረን የስልክ ውይይት፣ የሁለቱን ሀገራት ሕዝቦች ከኮቪድ 19 በኋላ ለሚፈጠረው የዓለም ሁኔታ ለማዘጋጀት፣ ዓለም አቀፋዊ እና የተቀናጀ አመራር እጅግ አስፈላጊ እንደ ሆነ ተነጋግረናል” ብለዋል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

