Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ለርዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሚ የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላለፉ 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) የርዋንዳ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን ለ4ኛ ጊዜ ላሸነፉት  ፖል ካጋሚ የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ፕሬዚዳንት ካጋሚ ቀጣዩ የሥራ ጊዜያቸው ውጤታማ እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡

በቀጣዩ የአመራር ጊዜያቸው ለርዋንዳ የላቀ መረጋጋት እና ልማት እንዲያመጡም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version