Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ ጋር ተወያዩ፡፡

ኢትዮጵያ በክብር በምታስተናግደው የ2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓቶች ጉባኤ እንኳን በደህና መጡ ሲሉም ለፕሬዚዳንቱ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ጥልቅ መሠረት ያለው ታሪካዊ፣ ባሕላዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ትስስርን የሚጋሩ ሀገራት መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ይህንን የሀገራቱን ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር መሥራታቻንን እንቀጥላለንም ነው ያሉት፡፡

Exit mobile version