አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያበለጸገው ከወረቀት ንክኪ ነጻ የሆነ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ቴክኖሎጂ በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ ቴክኖሎጂው የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡
አሁን ላይም ቴክኖሎጂው በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት፣ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና በፕላንና ልማት ሚኒስቴር እየተተገበረ ይገኛል ብለዋል፡፡
በቀጣይ ወደ ሌሎች ተቋማት እና ክልሎች የማስፋፋቱ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ሚኒስትሩ ያስገነዘቡት፡፡
የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ ቴክኖሎጂው ኮሚሽኑ እያከናወናቸው ለሚገኙ የሪፎርም ሥራዎች ትግበራ አጋዥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የመንግስትን አገልግሎት በማቀላጠፍ የዜጎችን እርካታ የሚያረጋግጥ ነው ያሉት ደግሞ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሰው ሃብት ልማት ሥምሪትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ናቸው።
ቴክኖሎጂው ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ለተጀመረው ጥረት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተመላክቷል።
በወንድሙ አዱኛ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!