Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የመስቀል በዓል በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመስቀል በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ነው

በዓሉ በተለያዩ ሐይማኖታዊ እና ባህላዊ ሥነ ሥርዓቶች ነው በድምቀት እየተከበረ የሚገኘው።

በትናንትናው ዕለት የመስቀል ደመራ በመላ ሀገሪቱ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በደማቅ ሥነ ሥርዓት መከበሩ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በትናንትናው ዕለት በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት፥ በዓሉን በይቅርታ፣ በፍቅር፣ በመተሳሰብ እና በእርቅ ማክበር እንደሚገባ አሳስበዋል።

Exit mobile version