Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

2ኛው የኢትዮ ጂቡቲ የቢዝነስ ማስፋፊያ ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) “የሎጂስቲክስ አቅርቦት ለቀጣናዊ የቢዝነስ ትስስር” በሚል መሪ ሐሳብ ሁለተኛው የኢትዮ ጂቡቲ የቢዝነስ ማስፋፊያ ጉባዔ በጂቡቲ እየተካሄደ ነው።

ጉባዔው የኢትዮጵያ እና ጂቡቲን የሎጂስቲክስ ትብብር ለማሳደግ ያለመ ሲሆን÷ የኢትዮጵያ ንግድ ዘርፍ ማሕበራት ም/ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አይናለም አባይነህ (ዶ/ር)፣ የጅቡቲ ንግድና ቱሪዝም ሚኒስትር ሞሀመድ ዋርሳማ ዲሬህ እና የዘርፉ ተቋማት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ሎጂስቲክስ ዘርፍ ማሕበር ፕሬዚዳንት ኤልሳቤት ጌታሁን ጉባዔው በሎጂስቲክስ ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ ቀጣይነት ያለውን የቢዝነስ ዕድገት ለማፋጠን እንደሚረዳ ተናግረዋል።

ጉባዔው ለእድገትና ትራንስፎርሜሽን በሚፈጥረው ዕድል ለቀጣናው ተምሳሌታዊ ትብብር እንደሚሆን ጠቅሰዋል።

የጂቡቲ የንግድና ቱሪዝም ሚኒስትር ሞሀመድ ዋርሳማ ዲሬህ በበኩላቸው÷ ጉባዔው የሁለቱን ሀገራት የንግድ ትብብር በማሳደግ የኢትዮ ጂቡቲ ኮሪደርን ይበልጥ ውጤታማ የሚያደርግ መሆኑን አንስተዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል የትስስር፣ የዕውቀት ሽግግር እና ስትራቴጂካዊ ትብብር ለመፍጠር የሚያስችል መድረክ እንደሆነም ጠቁመዋል።

በመድረኩ የሎጂስቲክስ ዘርፉን አቅም ለማሳደግ መሰል ትብብሮች ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተጠቅሷል።

ጉባዔውን የኢትዮ ሎጂስቲክስ ዘርፍ ማሕበር ከኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት፣ ከጂቡቲ ንግድ ምክር ቤት እና ትሬድ ማርክ አፍሪካ ጋር በመተባበር ማዘጋጀታቸው ተገልጿል።

የቀጣናውን ሀገራት የሎጂስቲክስ ንግድ ትስስር ለማጠናከር ያለመው የመጀመሪያው ዙር መድረክ አዲስ አበባ ተካሂዷል።

በአሸናፊ ሽብሩ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version