አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2018 የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከብሮ ተጠናቅቋል አሉ የቱለማ አባገዳ ጎበና ሆላ፡፡
አባ ገዳ ጎበና በሰጡት መግለጫ ÷ የ2018 የሆረ ፊንፊኔ እና ሀርሰዴ ኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ ከተሞች የኢሬቻ በዓል በድምቀት እንዲከበር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡