የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከብሮ ተጠናቅቋል – አባገዳ ጎበና ሆላ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2018 የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከብሮ ተጠናቅቋል አሉ የቱለማ አባገዳ ጎበና ሆላ፡፡
አባ ገዳ ጎበና በሰጡት መግለጫ ÷ የ2018 የሆረ ፊንፊኔ እና ሀርሰዴ ኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ ከተሞች የኢሬቻ በዓል በድምቀት እንዲከበር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡