አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በነገው ዕለት በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል፡፡
ቀኑ “ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የሚከበረው፡፡
በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት መሰረት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት እና በሰንደቅ ዓላው መሀል ላይ የሚገኘው ዓርማ ትርጉም ምንድን ነው?
1. አረንጓዴው ቀለም፡- የሥራ፣ የልምላሜና የዕድገት ምልክት ነው፡፡
2. ቢጫው ቀለም፡- የተስፋ፣ የፍትሕና የእኩልነት ምልክት ነው፡፡
3. ቀዩ ቀለም ፡- ለነፃነትና ለእኩልነት መስፈን የሚደረግ የመስዋዕትነትና የጀግንነት ምልክት ነው፡፡
እንዲሁም በሰንደቅ ዓላማው መሀል ላይ የሚገኘው ዓርማ ትርጉም ከታች እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
1. ክብ የሆነው፡- ሰማያዊ መደብ ሰላምን ያመለክታል፡፡
2. ቀጥታና እኩል የሆኑት መስመሮች፡- የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንዲሁም የሐይማኖቶችን እኩልነት ያመለክታሉ፡፡
3. ቀጥታና እኩል ከሆኑት መስመሮች የተዋቀረው ኮከብ፡- የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በመፈቃቀድ የመሠረቱትን አንድነት ያመላክታል፡፡
4. ቢጫ ጨረሩ ደግሞ ፡- በመፈቃቀድ አንድነት ለመሰረቱት ብሔር፣ ብሔረሰቦች የፈነጠቀውን ብሩህ ተስፋ ይጠቁማል፡፡
በአቤል ነዋይ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!