አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጤና ሚኒስቴር የመድኃኒት አቅርቦት እና የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳለጥ ጤንነቴ የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ አደረገ።
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በመተግበሪያው ምረቃ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት÷ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።
መንግስት በሽታን ከመከላከል ባሻገር አክሞ በማዳን ስራ ላይ በትኩረት እየሰራ እንደሆነና ውጤትም እየተመዘገበ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው ዛሬ ይፋ የተደረገው መተግበሪያ ከፍተኛ ጥራት እንዳለው አንስተው÷ ታካሚ ተኮር እንደሆነም አመላክተዋል፡፡
የጤናውን ዘርፍ ተደራሽና ቀልጣፋ ለማድረግ ቴክኖሎጂ ወሳኝ መሆኑን ገልጸው÷ ሚኒስቴሩ የዜጎችን የጤና አገልግሎት ለማሻሻል የተለያዩ ስትራቴጂዎችን ነድፎ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ሚኒስቴሩ በቅርቡ ባስተዋወቀው አዲሱ የጤና ፖሊሲ ከመከላከል ባሻገር አክሞ ማዳን ላይ ትኩረት በማድረግ በሀገሪቱ የጤና ሁኔታን ለመከታተልና ለመጠበቅ እየሰራ ይገኛል፡፡
በቅድስት ተስፋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

