አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያና ማሌዢያ የንግድና ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በወሳኝ የልማት መስኮች ትብብራቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ።
የኢትዮጵያና ማሌዢያ ከፍተኛ የቢዝነስ ፎረም በዛሬው ዕለት በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ተካሂዷል።
በፎረሙ የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የንግድና ኢንቨስትመንት አልሚ ባለሃብቶች ተገኝተዋል።
ፕሬዚዳንት ታዬ በመድረኩ እንዳሉት፥ የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጉብኝት በሀገራቱ መካከል ያለውን የንግድ ትስስር በማጠናከር የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን ለማጎልበት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።
ኢትዮጵያና ማሌዢያ ያላቸው የብዝኅ ሕብረ ብሔራዊነት እሴቶች ለጋራ ዕድገትና ቀጣናዊ ትብብር ልዩ ዕድል መሆናቸውን ገልጸዋል።
በፈረንጆቹ 1965 የተጀመረውን የሀገራቱን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በንግድና ኢንቨስትመንት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በማድረግ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ የኢንቨስትመንት ሥነ ምኅዳር መገንባቷን ጠቅሰው፤ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በትክክለኛ የልማት መንገድ ላይ እየተጓዘች ትገኛለች ብለዋል።
የማሌዢያ ኩባንያዎች የኢትዮጵያን የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎች የሚጠቀሙበት ምቹ ምኅዳር መኖሩን አስረድተዋል።
ሀገራቱ በግብርና፣ በማዕድንና በሌሎች ወሳኝ የልማት መስኮች ያላቸውን የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
የማሌዢያ ኩባንያዎች የኢትዮጵያን የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎች በመጠቀም የጋራ ብልጽግና እና ተጠቃሚነትን የሚወስን የልማት ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

