አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ታማኝ ግብር ከፋዮች ገበያን በማረጋጋት ረገድ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል አሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)።
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት 3ኛ ዙር የግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች የእውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብር ተካሂዷል።
ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት ÷ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ካደጉ ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ ለማድረግ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡
በክልሉ በግብርና፣ ኢንዱስትሪና በሌሎች ዘርፎች የሚሳተፉ አልሚዎችን የማበረታታቱና የመደገፉ ሥራ ተጠናከሮ ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡
ግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች በመሆን እውቅናና ሽልማት የተበረከተላቸው ታማኝ ግብር ከፋዮች ብቻ ሳይሆኑ አምራች፣ አቅራቢና ገበያ የሚያረጋጉ ናቸው ሲሉ አውስተዋል፡፡
በክልሉ በተለያዩ ዘርፎች መሰማራት ለሚፈልጉ ባለሃብቶች ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ጠቁመው÷ አልሚዎች ዕድሉን በመጠቀም በልማት ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ ጠይቀዋል፡፡
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ሕይወት አሰግድ በበኩላቸው÷ በክልሉ የሚሰበሰበው ገቢ በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን የተለያዩ የአሰራር ሥርዓቶች እየተዘረጉ ነው ብለዋል፡፡
ክልላዊ የገቢ አቅሞችን በጥናት በመለየት የገቢ አፈጻጸምን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ማለታቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ የሽዋስ አለሙ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

