አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር መመለስ ላይ በሚታዩ ክፍተቶች ዙሪያ ከቡና፣ ሰሊጥ እና ጥራጥሬ ላኪዎች ጋር ተወያይተዋል።
በምክክር መድረኩ ባንኩ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ገቢ የመጠበቅ እና የኤክስፖርት ገቢ በወቅቱ እና በግልጸኝነት እንዲመለስ የማድረግ ሃላፊነት እንዳለበት ተመላክቷል፡፡
ብሔራዊ ባንክ ከሕጋዊ ርምጃ በፊት ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ገንቢ ውይይት ማድረግን እንደሚያስቀድም ተጠቅሷል፡፡
ባንኩ ተግዳሮቶችን ለመፍታት፣ ተገዢነትን ለማሻሻል እና የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ለማስጠበቅ ከግል ዘርፉ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ከዚህ ባለፈም ተጠያቂነትና ኃላፊነት የሚሰማው የወጪ ንግድ ልምዶችን የማበረታታት እና የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓቱን የማሳደግ ሥራውን እንደሚያጠናክር አጽንኦት ሰጥቷል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

