አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ሽብርተኝነትና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል ቁርጠኛ ናት አሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ፡፡
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከአምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ሀገራቱ በፖሊስ ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር፣ ሽብርተኝነትንና ሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል
እንዲሁም በልምድ ልውውጥ፣ በአቅም ግንባታ እና በሌሎች በዘርፎች ላይ በትብብር ለመስራት መወያየታቸውን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር በፖሊስ ዘርፍ ያላትን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ከፍተኛ ፍላጎት አላት፡፡
በተለይም ዋሽንግተን ሽብርተኝነትና ሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ እና በትብብር ለመከላከል ቁርጠኛ መሆኗን ነው ያረጋገጡት፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

