Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር በፖሊስ ዘርፍ ያላትን ትብብር ይበልጥ ታጠናክራለች – አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋን

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ሽብርተኝነትና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል ቁርጠኛ ናት አሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከአምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ሀገራቱ በፖሊስ ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር፣ ሽብርተኝነትንና ሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል

እንዲሁም በልምድ ልውውጥ፣ በአቅም ግንባታ እና በሌሎች በዘርፎች ላይ በትብብር ለመስራት መወያየታቸውን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

‎አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር በፖሊስ ዘርፍ ያላትን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ከፍተኛ ፍላጎት አላት፡፡

በተለይም ዋሽንግተን ሽብርተኝነትና ሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ እና በትብብር ለመከላከል ቁርጠኛ መሆኗን ነው ያረጋገጡት፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.