አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መካኒሳ አካባቢ የሚገኘውን ቢላሉል ሐበሺ በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ እንዳሉት ÷ ቢላሉል ሐበሺ የኢትዮጵያ ታሪክ አካል የሆነውን የኢትዮጵያን የእስልምና ጉዞ ከመነሻ እስካሁን የሚያሳይ ሙዚዬም አደራጅቷል።
በሀገራችን የእስልምና ታሪካችንን የሚዘክሩ ሙዚዬሞች በጣት የሚቆጠሩ በመሆናቸው ይህ ሙዚዬም ታላቅ ዋጋ ያለው መሆኑን አውስተዋል፡፡
በሙዚዬሙ ውስጥ ከመጀመሪያው ሒጅራ አንሥቶ እስካሁን ያለው ታሪካችን በሚገባ ይታያል ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን፡፡
ኢትዮጵያ የብዙ ሶሐባዎች ማረፊያ፣ የታላላቅ ዓሊሞች መገኛ፣ የአስደናቂ እስላማዊ ቅርሶች መናኸሪያ መሆኗንም ነው ያስገነዘቡት፡፡
ተቋሙ ወጣቶችን በሙያ አሠልጥኖ ለሥራ በማብቃት፣ ችግረኞችን በመርዳት፣ ጥናትና ምርምርን በመደገፍ፣ ለወጣቶች ተስማሚ መዋያ በማዘጋጀት የሚያደርገው አስተዋጽኦ እጅግ ታላቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ቢላሉ ሐበሺ ዕድሮች አሁን ከያዙት ዓላማ በላይ በማከናወን የማኅበረሰብን ሕይወት ሊቀይሩ እንደሚችሉ አርአያ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ስለሆነም ተቋሙን በማገዝ ታሪካችንን መጠበቅና ወጣቶቻችንን ማብቃት አለብን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

