አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ሕልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ በድንገት በማረፉ ኀዘን ተሰምቶኛል ብለዋል።
ነጻነት በተለይም በሕዳሴ ግድብ በተዘጋጀው የ2016 አዲስ ዓመት የመቀበያ ፕሮግራም የነበረውን አስተዋጽዖ ሁሌም አስታውሰዋለሁ ነው ያሉት።
ሁላችንም አዲሱን ዓመት በደስታ እንድንቀበል አድርጎን ነበር በማለት ገልጸው፤ ለቤተሰቦቹ እና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን ተመኝተዋል።

