አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነዳጅን በቁጠባና ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም ይኖርብናል አሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንዳሉት፥ በመካከለኛው ምሥራቅ በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት ነዳጅ ገዝተው የሚጠቀሙ ሀገሮች እንደልብ ለማግኘት ተቸግረዋል።
በመሆኑም ችግሩ ተፈቶ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት እስኪመለስ ድረስ ነዳጅን በቁጠባና ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የነዳጅ አከፋፋዮች፣ ማደያዎችና ተጠቃሚዎች ነዳጅን በቁጠባ፣ ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት ሁሉም በኃላፊነት ስሜት ሊጠቀም ይገባል ነው ያሉት፡፡

