Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የክረምት በጎ ፈቃድ ዘመቻ በይፋ አስጀመሩ

‎አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀገራችንን በጋራ ማንሳት የምንችለው አንዳችን ለሌላችን እጃችንን ስንዘረጋ ብቻ ነው አሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)‎ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ጎሮ ወረዳ የዘንድሮውን የክረምት የበጎ ፈቃድ ዘመቻ በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ የክረምቱ ወቅት ሲደርስ፣ እኛም ለወገኖቻችን የምንዘረጋው የደግነት እጅ አብሮ ይጀግናል ብለዋል፡፡

‎በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ጎሮ ወረዳ የዘንድሮውን የክረምት የበጎ ፈቃድ ዘመቻ ማስጀመራቸውን ነው የገለጹት፡፡

የገጠር ኮሪደር ልማት መርሐ ግብር አካል በሆነው ዲዛይን መሠረት 20 ቤቶች በአካባቢው እንደሚገነቡም አብራርተዋል፡፡

‎ሀገራችንን በጋራ ማንሳት የምንችለው አንዳችን ለሌላችን እጃችንን ስንዘረጋ ብቻ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በዚህ ሥራ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Exit mobile version