Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነታችን ምሰሶ ነው – አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነታችን ምሰሶ ነው አሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ።
ጳጉሜን 5 “የነገ ቀን” በሳይንስ ሙዚዬም የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው።
አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ በዚህ ወቅት÷ የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት መሆኑን አውስተዋል።
የቴክኖሎጂ አጠቃቀም የዓለምን የውድድር ካርታ እንደገና እየሳለ እንደሚገኝ ጠቁመው ÷ ለኢትዮጵያም የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የላቀ ፍጥነት፣ የትግበራ ጥንካሬ እና የተቋማት ቅንጅትን የሚሹ ናቸው ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያውያን በሃሳብ በማይስማሙባቸው ጉዳዮች ላይ ቁጭ ብለው በመምከር አዲስ የምክክር ባህልን እያዳበሩ እንደሚገኙም አፈ ጉባዔው ተናግረዋል።
በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ የኢትዮጵያን የዲጂታል ሽግግር እውን ለማድረግ በርካታ ሥራዎች እየተተገበሩ እንደሚገኙ አመልክተዋል።
ለዚህ ውጤታማነት የተጠናቀቀው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ጉልህ ድርሻ እንደነበረው ጠቁመው ÷ ይህ ጅማሮ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በአሸናፊ ሽብሩ
Exit mobile version