አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ተቀማጭ የውጭ ምንዛሬ ክምችታችን ከ20 በመቶ በላይ አድጓል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የውጭ ምንዛሪን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፤ ከሪፎርም በፊት በባንክ ስርዓት እና በትይዩ ገበያው መካከል የነበረው የገንዘብ ልውውጥ ወደ 110 በመቶ ልዩነት ነበረው ብለዋል።
ነገር ግን በሪፎርሙ ምክንያት በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ወደ 13 በመቶ ዝቅ ማለቱን ገልጸው፤ ይህም በጣም ጤነኛ ምልክት መሆኑን እንደሚያሳይ ተናግረዋል።
ባለፈው ዓመት 33 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ በላይ ማስገባት መቻሉን አስታውሰው፤ በዚህም ምክንያት ተቀማጭ የውጭ ምንዛሪ ክምችታችን ከ20 በመቶ በላይ አድጓል ብለዋል፡፡
የወጪ ንግድ፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እና ሀዋላ አድገዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የእዳ ጫና ሽግሽግ ስለተሰራ ወደ መካከለኛ ደረጃ መጥቷል ነው ያሉት።
እነዚህ ስኬቶች የሪፎረሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ የማይጠበቁ አመርቂ ውጤቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።
#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ
በቴዎድሮስ ሳህለ

