Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሚመራ የልዑካን ቡድን ጁባ ገባ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 23 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሚመራ የልዑካን ቡድን ዛሬ ደቡብ ሱዳን ጁባ ገብቷል።

የልኡካን ቡድኑ ጁባ የገባው በሱዳን የሽግግር መንግስትና በተቃዋሚ ኃይሎች መካከል የሚፈረመው የሰላም ስምምነት  ላይ ለመታደም ነው።

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጁባ ሲደርሱ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ለአንድ ዓመት ያህል ሁለቱን ቡድኖች ሲያደራድሩ መቆየታቸውን ከኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

Exit mobile version