በሩብ ዓመቱ 73 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰብስቧል
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2014 ዓ.ም ሩብ ዓመት 73 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ሰላማዊት ካሳ በ2014 ዓ.ም 407 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን አስታውሰው በሩብ ዓመቱ 73 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡
ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች፣ ከልማት ትብብር ተቋማትም 369 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር መገኘቱን አስታውቀዋል፡፡
ምጣኔ ሃብታዊው ጤናማ እንዲሆን በርካታ ስራዎች እተሰሩ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትር ዲኤታዋ በመሰረታዊ ፍጆታዎች ላይ መሻሻል መታየቱን ገልፀዋል፡፡
መንግስትም እነዚህ መሰረታዊ ፍጆታዎች ላይ የሚያደርገውን ድጎማ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።
በ2014 በጀት ዓመትም የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
በሌላ በኩል የበጀት ሽግሽግ ማድረግ፣ አገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ፕሮጀክቶች ላይ ጠንካራ ክትትል ማድረግ የማክሮ ኢኮኖሚው የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታዋ፡፡
የመንግስትን ሃብት በቁጠባ እና ለታለመለት ዓላማ ለመጠቀም እየተሰራ መሆኑን በመጥቀስም፥ የብድር ጫናው እንዳይባባስም በተለይ ከአበዳሪ አካላት ጋር የእዳ ማሸጋሸግ ድርድሮች እየተከናወኑ ነው ብለዋል፡፡
በዚህ ረገድ እየተደረጉ ያሉ ስራዎችም ውጤት እያመጡ ነው ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታዋ፡፡
ህብረተሰቡ በግንባር ደጀንነቱን ሲገልፅ ቆይቷል ያሉት ሚኒስትር ዲኤታዋ ሌላው ግንባር የኢኮኖሚ ነውና ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለአላስፈላጊ ወጪ የሚዳርጉ ተግባራትን በመቀነስ ህብረተሰቡ ደጀንነቱን በዚህም እንዲያረጋግጥ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በፌቨን ቢሻው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን