Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ማንቸስተር ሲቲ ከ115 ክሶች መካከል በ114ቱ ጥፋተኛ ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቸስተር ሲቲ በፕሪሚየር ሊጉ የፋይናንስ ሕጎችን በመጣስ ከቀረቡበት 115 ክሶች መካከል በ114ቱ ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል። ፕሪሚየር ሊጉ ከፈረንጆቹ 2009 እስከ 2018 ባሉት ዘጠኝ ዓመታት ውስጥ የሊጉን የፋይናንስ ሕጎች ጥሷል በሚል 115 ክሶችን መሥርቶበት ነበር። ክሶቹ በክለቡ የገንዘብ መረጃ አቀራረብ፣ የስፖንሰርሺፕ ገቢዎችና ከተጫዋቾች እና አሰልጣኞች ክፍያ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮሩ ሲሆን ክለቡ በፕሪሚየር ሊጉ ምርመራ ወቅት በቂ ትብብር አላደረገም የሚል ክስም…
Read More...

ሚኬል አርቴታ ከአርሰናል ጋር ውሉን ለማደስ ተስማማ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ጋር የተሻሻለ አዲስ ውል ለመፈራረም ተስማምቷል። ስፔናዊው አሰልጣኝ ከአርሰናል ጋር ያለው ኮንትራት በዚህ የውድድር ዘመን መጨረሻ የሚያበቃ ሲሆን ከክለቡ ጋር ስለሚኖረው የወደፊት ቆይታ ላለፉት በርካታ ወራት ድርድር ሲካሄድ ቆይቷል።…

እግር ኳስን ለማቆም ጫፍ ደርሶ የነበረው ኮከብ – ራፊንሃ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የቢቢሲ ስፖርት አምደኛው ጊሌም ባላጌ፥ ብራዚላዊው ኮከብ "የእግር ኳስ ህልሜ አክትሞለታል" የሚል ውሳኔ ላይ የደረሰበትን አጋጣሚ ወደ ኋላ መለስ ብሎ ይተርካል። በብራዚሏ ፖርቶ አሌግሪ ከተማ የተወለደው ራፋኤል ዲያዝ ቤሎሊ (ራፊንሃ) እግር ኳስን የጀመረው እንደ አብዛኞቹ ተጫዋቾች ለኳስ ባለው ፍቅር ብቻ አልነበረም።…

ማንቼስተር ዩናይትድና ፉልሃም አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ ከፉልሃም ጋር 1 አቻ ተለያይቷል፡፡ ምሽት 12:30 በክራቫን ኮቴጅ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ፉልሃም ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በራሱ ላይ በስቆጠራት ግብ መምራት ችሎ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ማቲያስ ኩኛ በጨዋታው መገባደጃ ላይ ባስቆጠራት…

አትሌቲኮ ማድሪድ ሪያል ማድሪድን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ179 ኛው የማድሪድ ደርቢ አትሌቲኮ ማድሪድ ሪያል ማድሪድን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡ ምሽት11 ሰዓት በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አሊያንድሮ ጊርማልዶ እና ጆናታን ዴቪድ ለአትሌቲኮ እንዲሁም አንቶኒዮ ሩዲገር ለሪያል ማድሪድ አስቆጥረዋል፡፡ በጨዋታው የሪያል ማድሪዱ ተከላካይ ዲያን ሁይሰን በጨዋታ ላይ…

ማንቼስተር ሲቲና ሊቨርፑል ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ  መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል ድል ቀንቷቸዋል፡፡ ቀን 10 ሰዓት ላይ በሜዳው ኢቲሃድ ሰንደርላንድን ያስተናገደው ማንቼሰተር ሲቲ 5 ለ 3 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ አስገራሚ ፉክክር በታየበት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ አንቶዋን ሴሜኒዮ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር÷  ኤንዞ…

ኢትዮጵያ በዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በዴንማርክ ኮፐንሃገን በተካሄደው ሁለተኛው የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች። ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ሻምፒዮና ዛሬ ፍጻሜውን ያገኘ ሲሆን ÷ ከ86 ሀገራት የተወጣጡ ከ450 በላይ አትሌቶች ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ላይ በወንዶችና በሴቶች ግማሽ ማራቶን፣…