ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አ.ማ
ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አ.ማ የቀድሞዎቹ ፋና እና ዋልታ በውህደት የፈጠሩት ጠንካራ ተቋም ነው፡፡ በሚሰራቸው ዜናዎች እና ፕሮግራሞች ሰው ተኮርና ተፅዕኖ ፈጣሪ ሚዲያ ሲሆን በዚህም በርካታ አድማጭ፣ ተመልካች እና ተከታዮችን ማፍራት ችሏል፡፡
በዲጂታል ሚዲያ አማራጮች፣ በፋና ቴሌቪዥን እና በፋና ፕላስ የቴሌቪዥን ቻናሎች፣ በብሔራዊ ሬዲዮ፣ በአዲስ አበባ 98.1 እና በብዝሃ ልሳን 105.3፣ ጅማ 98.1፣ ጎንደር 98.1፣ ደሴ 96.0፣ ሐሮማያ 94.8፣ ሻሸመኔ 103.4፣ ወላይታ ሶዶ 99.9፣ ነቀምቴ 96.1፣ ደብረብርሃን 94.0፣ አሰላ 90.0 እና በሚዛን አማን 92.5 ኤፍኤሞች የሚያሰራጫቸው ይዘቶች ተደራሽነትን ከተወዳጅነት ጋር እንዲያተርፍ አድርገውታል፡፡
ተቋማችን አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ አፋርኛ፣ ሶማሊኛ፣ ትግርኛ፣ ወላይትኛ፣ ሲዳምኛ፣ አረብኛ እና እንግሊዝኛን የስርጭት ቋንቋዎቹ በማድረግ ለኢትዮጵያውያን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ብልፅግና የሚተጋ ኢትዮጵያዊ ሚዲያ ነው፡፡
በይዘት ካለው ተወዳጅነት በተጨማሪ በሚዲያ ግንባታና ማቋቋም እንዲሁም በስልጠናና ማማከርም ስመ ጥር ተቋም ነው፡፡
ኢትዮጵያን እናበሥራለን