Fana: At a Speed of Life!

የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት 4 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ ወደ አገር ውስጥ ገብቷል- የንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን

አዲስ አበባ ፣ህዳር 22፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ ) የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ካቀደው 8 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ ውስጥ በመጀመሪያ ዙር 4 ሚሊየን ኩንታል ማስገባቱን የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን አስታወቀ

ተጨማሪ 4 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ በሚቀጥሉት 15 ቀናት ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አቻ ደምሴ የተናገሩ ሲሆን÷ ምርቱ በአዳማ ፣ ሻሸመኔ ፣ባህርዳር ፣ድሬዳዋ እና አዲስ አበባ በሚገኙ የኮርፖሬሽኑ አምስት ማዕከላት እንደሚሰራጭ ገልጸዋል።

ስርጭቱ በሚቀጥሉት 15 ቀናት በተጠቀሱት ማዕከላት እንደሚከናወን እና የሚገባው ቦታ መድረሱን የሚከታተል ኮሚቴ ተዋቅሮ ቁጥጥር እንደሚደረግ ዋና ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል።

11 ቢሊየን ብር ወጪ የተደረገበት የስንዴ ምርት በዳቦ ቤቶች ላይ የሚታየውን የዋጋ ጭማሪ እና የዱቄት እጥረት ለመቅረፍ ሚናው የጎላ ነውም ብለዋል።

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎችን በመደገፍ በአገሪቷ ላይ የተቃጣውን የኢኮኖሚ ጦርነት ለመመከት እንደሚረዳም ጭምር አብራርተዋል።

ኮርፖሬሽኑ የአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የሰብል ምርቶችን የምርት ብዛት ከሚታይባቸው ቦታዎች በማንሳት እጥረት ወዳለበት ቦታ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን አመላክተዋል።

በተመሳሳይ ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ለማድረስ ኮርፖሬሽኑ ከአጋር አካላት ጋር እየሰራ እንደሆነና በቅርቡ ምላሽ እንደሚያገኝ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.