Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት ተጨማሪ 136 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ5 ሺህ 616 ዜጎች በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ 136 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
 
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ እንዳስታወቁት÷ባለፉት 24 ሰዓታት 16 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
 
በሌላ በኩል 87 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን÷234 ዜጎች ደግሞ በጽኑ ህክምና ክፍል ውስጥ እንደሚገኙ ነው የገለጹት፡፡
 
በአጠቃላይ እስካሁን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 371 ሺህ 672 መድረሱ ተመላክቷል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.