Fana: At a Speed of Life!

የገቢ አሰባሰቡን በሚጎዳ ሕገ ወጥ ተግባር ተሰማርተው የነበሩ 63 ድርጅቶች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር ለአራት ወራት ባደረገው ምርመራ ከታክስ አስተዳደር ተሰውረው ሐሰተኛ ግብይት ሲያከናውኑ የነበሩ እና በሕገ ወጥ መንገድ የካሽ ሬጂስተር ማሽን ሲጠቀሙ የነበሩ 63 ድርጅቶች መያዛቸውን አስታውቋል።

በክትትል የተደረሰባቸው ሕገ ወጥ ድርጅቶች መከፈል የነበረበት ግብር እንዲሰወር በማድረግ በገቢ አሰባሰቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል ነው የተባለው፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ 20 ሕገ ወጥ የካሽ ሬጂስተር ማሽኖችም መያዛቸው ተገልጿል፡፡

በሕገ ወጥ ተግባሩ ተሳትፎ ሊኖራቸው ይችላል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በሕግ እየታየ እንደሚገኝ ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሀገራቸውን የሚወዱ ከሠሩት ብቻ ሳይሆን ከራሳቸው ሳይሰስቱ በሚሰጡበት በዚህ ወቅት እንደዚህ ዓይነት ሕገ ወጥ ድርጅቶች ደግሞ ከእናት ሀገራቸው መሰርቃቸው ተገቢ አለመሆኑም ተመላክቷል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.