የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ጽህፈት ቤት እና የሲዳማ ክልል ለመከላከያ ሰራዊት ከ70 ሚሊየን ብር ባላይ ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ጽህፈት ቤት እና የሲዳማ ክልል ለመከላከያ ሰራዊት ያዘጋጁትን ከ70 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የገንዘብና የአይነት ድጋፍ የመከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሊዊጂ በተገኙበት አስረክበዋል፡፡
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት ጽህፈትቤት ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት 10 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ እንደገለጹት ድጋፉ÷ የተለያዩ ወጭዎችን በመቀነስ ከዓመታዊ በጀት እና ከሰራተኞች ደመወዝ የተሰበሰበ ነው፡፡
በተመሳሳይ የሲዳማ ክልል ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ከ60 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡
ክልሉ በጥሬ ገንዘብ 50 ሚሊየን ብር እና በአይነት 317 ሰንጋዎች፣ 617 በጎችና ፍየሎች፣ ደረቅ ስንቅ እና የተለያዩ የህክምና ቁሰቁሶችን ነው በድጋፍ መልክ ለመከላከያ ሰራዊት ያስረከበው፡፡
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ÷ ጦርነቱ የመላውን ኢትዮጵያን ሕዝብ የሚመለከት በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ መከላከያ ሰራዊትን መደገፍ አለበት ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የመከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሊዊጂ ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት እንደገለጹት÷ የሲዳማ ክልል እና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤትና ሰራተኞች ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት በጦር ሀይሎች ኮምፕሪሄንሲቭ ሆስፒታል በመገኘት የሰንጋ፣ የመፅሐፍና ሌሎች ድጋፎችን አበርክቷል፡፡
የባህልና ስፖርት ሚንስትሩ ቀጀላ መርዳሳ አባቶቻችን በነፃነት ያቆዩልንን ሀገር ጠብቀን በማቆየት ለመጪው ትውልድ ልናስረክብ ይገባል ብለዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የሆስፒታሉ አዛዥ ዶ/ር ብ/ጄ ሀይሉ እንዳሻው÷ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!