የኮቪድ-19 ክትባት የጎንዮሽ ክስተት ሪፖርት ማድረጊያ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ተደረገ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 24 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮቪድ-19 ክትባት የጎንዮሽ ክስተት ሪፖርት ማድረጊያ የሞባይል መተግበሪያ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ።
ማስጀመሪያ ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አዘጋጅነት መካሄዱን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።
ይህ የአንድሮይድ መተግበሪያ ክትባትን ተከትሎ የሚመጡ ተያያዥ የጎንዮሽ ክስተቶች መረጃን በጤና ባለሙያዎች ለመያዝ፣ ለመተንተንና ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ እንዲሁም የኮቪድ -19 ክትባት ደህንነት ክትትል ለማገዝ እንዲውል የተዘጋጀ ነው ተብሏል።
ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ይህ መተግበሪያ እንዲዘጋጅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች ምስጋና አቅርበዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!