አሸባሪው ህወሓት በላልይበላ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የከፋ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 26፣ (2014) አሸባሪው ቡድን በላልይበላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ያደረሰው ውድመት ቡድኑ ጸረ- ኢትዮጵያ መሆኑን በተግባር ያረጋገጠበት መሆኑን የጋይነት ጋሸና ግንባር ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ አቶ ሲሳይ ዳምጤ ገልጸዋል፡፡
ቡድን ላልይበላን ወርሮ በቆየበት ወራት የላልይበላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መሰረተ ልማቶችን በከፍተኛ ሁኔታ ማውደሙን የገለጹት አስተባባሪው ÷ ድርጊቱ ቡድኑ ኢትዮጵያ ላይ ያለውን ጥላቻ በተግባር ያረጋገጠበት ነው ብለዋል፡፡
የላልይበላ አብያተ ክርስቲያናት የዓለሙ ማህበረሰብ የሚገለገልበት ሃይማኖታዊ እና ታሪካዊ ስፍራ መሆኑን አንስተው ÷ የቡድን አሸባሪነት በአገር አቀፍ ብቻ ሳይሆን በዓለም ላይ ጫና የሚያሳድር መሆኑን እንደሚያሳይም ነው አቶ ሲሳይ የገለጹት፡፡
አክለውም ኢትዮጵያ ከሌሎች ዘርፎች በተጨማሪ አገሪቱ ያላትን ታሪካዊ እና ትውፊታዊ ሃብት በማውደም ወደኋላ እንድትሄድ ያደረገው ጥረት ነውም ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጠላት መሆኑን በተግባር እያረጋገጠ ያለውን ወራሪ ቡድን ÷ በተንቀሳቀሰበት ሁሉ በመደምሰስ በአጭር ጊዜ ማጥፋት እንደሚገባም የኮማንድ ፖስቱ አስተባባሪ አስታውቀዋል፡፡
በተጨማሪም በአሸባሪው የወደመውን መሰረተ ልማት ድጋሚ በመገንባት ልማቱ እንደሚቀጥል መናጋራቸውን አሚኮ በዘገባው አመላክቷል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!