ለሸኔ ታጣቂ ሊተላለፍ የነበረ ከ 2 ሺህ በላይ የብሬን ጥይት ዓለም ገና ከተማ ላይ ተያዘ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መነሻን አዋሽ አርባ ባደረገ የቤት መኪና ውስጥ ተደብቆ ለሸኔ ታጣቂ ሊተላለፍ የነበረ 2 ሺህ 560 የብሬን ጥይት ተያዘ።
ጥይቱ ዓለም ገና ከተማ ላይ መያዙ ነው የተመለከተው።
ኅብረተሰቡ ያደረሰውን ጥቆማ መሠረት አድርጎ የኦሮሚያ ፖሊስ ባደረገው ክትትል የብሬን ጥይቱ ተይዟል።