Fana: At a Speed of Life!

በዓሉ ህወሓት የገነባውን የመለያየት ግምብ በማፍረስ በመደመር ሕብረ-ብሔራዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ቃል ኪዳናችንን የምናድስበት መሆን አለበት-አቶ ሽመልስ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ህወሓት የገነባውን የጥላቻና የመለያየት ግምብ በማፍረስ በመደመር እሳቤ አንድነታችን በማጠናከር ምቹ የሆነች ሕብረ-ብሔራዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ቃልኪዳናችንን የምናድስበት መሆን አለበት አሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፡፡
 
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የ16ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓልን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
 
በመልዕክታቸውም ሕዳር 29 ቀን የኢፌዴሪ ሕገመንግሥት የጸደቀበት፤ የማንነት፣ ባህል፣ እሴት፣ ቋንቋና ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ዋስትና ያገኘበት ቀን በመሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ ታሪካዊ ዕለት ነው ብለዋል፡፡
 
ይህንን በዓል ስናከብር ላለፉት 27 ዓመታት ህወሓት በመካከላችን የገነባውን የጥላቻና የመለያየት ግምብ በማፍረስ፣ በመደመር እሳቤ አንድነታችንን በማጠናከር የበለጸገችና ለሁላችን ምቹ የሆነች ሕብረ-ብሔራዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ቃልኪዳናችንን የምናድስበት መሆን አለበትም ነው ያሉት፡፡
 
ብዝሃነታችን፤ ኢትዮጵያዊ ውበታችን በዓለም ላይ ደምቆ እንዲታይ የሚያደርግ የጥንካሬያችን መገለጫ እንጂ የመለያየት ምንጭ ሊሆን እንደማይችልም አንስተዋል፡፡
 
ይሁን እንጂ ለሴራ የተፈጠረና በሴራ ያደገው የህወሓት ቡድን ብዝሃነታችንን ለእኩይ አላማው በመጠቀም በህዝቦች መካከል መልካም ግንኙነት እንዳይኖር፣ አንድነትና ወንድማማችነት እንዳይጎለብት በማድረግ ጥርጣሬና መለያየት እንዲሰፍን ሳይታክት ሲሰራ መኖሩን ነው ያስታወሱት፡፡
 
በይስሙላ የፌዴራላዊ ሥርዓት ህዝቦችን በመሸንገል ራስን በራስ የማስተዳደር ሕገ-መንግሥታዊ መብትን በመጣስና ኢ-ፍትሐዊነትን በመዘርጋት የጥቂት ቡድን የበላይነት እንዲሰፍን አድረጓልም ብለዋል፡፡
 
ይህ በሴራ ፖለቲካ ውስጥ ተወልዶ ያደገው ቡድን በኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የጋራ ተጋድሎ ከስልጣን ተሽቀንጥሮ ከተጣለ በኋላም ጭምር በህዝቦች መካከል መቃቃርና ግጭቶችን በማቀነባበርና በመደገፍ በንጹሃን ዜጎች ላይ ዘግናኝ ወንጀሎችን መፈጸሙ አልበቃ ብሎት፥ የውክልና ጦርነት በማካሄድ አገራችንን ለመበታተን ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር ተሰልፎ እየወጋን ይገኛል ነው ያሉት፡፡
 
የህወሓት የክህደት ተግባር የኢትዮጵያ ብሔሮቸ፤ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ለሀገራቸው ህልውና በአንድነት እንዲሰለፉ በማድረጉ ጠላቶቻችንን በመደምሰስ በድል ጎዳና ላይ እንገኛለን ሲሉም አንስተዋል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.