Fana: At a Speed of Life!

ባንኩ ዳያስፖራዎች ለጦርነቱ ተጎጂዎች ድጋፍ ማድረግ የሚችሉበት አሰራር አመቻቸ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ዳያስፖራዎች ህወሓት በከፈተው ጦርነት ተጎጂ ለሆኑ ወገኖች ድጋፍ ማድረግ የሚችሉበትን አሰራር አመቻቸ።

ባንኩ ዳያስፖራዎች ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ለተጎጂዎች ድጋፍ ማድረግ የሚችሉበት ክፍል ማዘጋጀቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል።

ድጋፍ ማድረጊያ ክፍሉ የዳያስፖራው ማህበረሰብ በተደጋጋሚ ያቀረበውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን፥ በ”ታላቁ ወደ ሃገር ቤት ጥሪ” ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላትም በአውሮፕላን ማረፊያው ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ ብለዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.