Fana: At a Speed of Life!

ምዕራባውያን ቻይና እና ሩሲያ ላይ የሚያሳርፉትን ጫና እንዲያቆሙ ፑቲን ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን የቻይና እና የሩሲያ ዕድገት በምዕራባዊያኑ ፖለቲካዊ ጫና እንደማይደናቀፍ አስታወቁ፡፡

ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን፥ ቻይና እና ሩሲያ በጠፈር ምርምር፣ ሕክምና፣ ሣይንሥ እና በመከላከያው ዘርፍ የላቀ የንግድ ትብብር መመሥረታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ቻይና የዓለም የኢኮኖሚ መሪነቱን ቦታ ከአሜሪካ እንደተረከበች፣ የመግዛት አቅሟም እየጨመረ እንደመጣ እና የትኛውም ኃይል ከፈጣን ዕድገቷ ሊገታት እንደማይችልም ተናግረዋል፡፡

ሩሲያ ከምዕራባዊያኑ ጋር የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ የፈረመችውን የነዳጅ ምርቷን የመቀነስ ስምምነትን እያከበረች ባለችበት ወቅት የነዳጅ ወጪንግዷን በ10 በመቶ ጨምራለች የሚል መሰረተ ቢስ ክሳቸውን ሀገራቱ እንዲያቆሙ ፑቲን ጠይቀዋል፡፡

ምዕራባዊያኑ በፈረንጆቹ 2022 በቻይና ቤጂንግ የሚካሄደውን የበጋ ኦሎምፒክ ፖለቲካዊ ገጽታ ከማላበስ እንዲቆጠቡም ፑቲን ጠይቀዋል፤ ቻይና ቁጥር አንድ አጋራችን ናት ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ቭላድሜር ፑቲን የታኅሣሥ ጋዜጣዊ ኮንፈረንሳቸውን ያካሄዱት በክሬምሊን ማኔዝ የሥብሰባ አዳራሽ ሲሆን፥ 507 ጋዜጠኞች ታዳሚ ሆነዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ፕሬዚዳንቱ 17 የታኅሣሥ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን የሰጡት በሞስኮ እንደነበርም ሲጂቲ ኤን አመላክቷል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.