ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አቡዳቢ ገብተዋል
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አቡዳቢ ገብተዋል።
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የአቡዳቢ ዘውዳዊ ልዑል እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መከላከያ ሰራዊት ምክትል ጠቅላይ አዛዥ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን አቀባበል አድርገውላቸዋል ።
ሁለቱ መሪዎች የሁለትዮሽ ግንኙታቸውን ማጠናከር በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ “ለእኔና ለልዑካን ቡድኔ ስለተደረገልን ደማቅ አቀባበል፣ ለወንድሜ ልዑል ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ነህያን ምስጋናዬ ይድረስ” ብለዋል።
በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸቸውን ገልጸው፥ በተጨማሪም የሁለቱ ሀገራት ትሥሥር የበለጠ በሚጠናከርበት መንገድ ላይ መምከራቸውን ጠቅሰዋል።
በአልአዛር ታደለ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!