Fana: At a Speed of Life!

በፈተናዎች ውስጥ ሆነን ታላላቅ ስራዎችን ሰርተናል- አቶ ብናልፍ አንዷለም

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ለሰላም ዘብ የሚቆም ዜጋ መፍጠር ፣ በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባት መፍጠር ፣ ህብረ ብሔራዊ አንድነት ማጠናከር እና የግጭት መከላከል ስርዓቶችን ማበጀት በእጅጉ ያስፈልጋል ሲሉ የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም ገለጹ።

ከጥር 22 እስከ 23 ቀን 2014 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው የፌዴራል፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር የሰላምና የፀጥታ ተቋማት የጋራ የምክክር መድረክ ተጠናቋል ።

በመድረኩ ማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም ፣ የብሔራዊ መረጃ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሐም በላይ ተገኝተዋል ።

አቶ ብናልፍ አንዷለም በማጠቃለያ ንግግራቸው በሀገራችን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ለሰላም ዘብ የሚቆም ዜጋ መፍጠር ፣ በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባት መፍጠር ፣ ህብረ ብሔራዊ አንድነት ማጠናከር እና የግጭት መከላከል ስርዓቶችን ማበጀት በእጅጉ ያስፈልጋል ብለዋል።

አሁን እንደ ሀገር በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ ብንሆንም በፈተናዎች ውስጥ ታላላቅ ስራዎችን ሰርተናል ያሉት አቶ ብናልፍ፥ ከሁሉም በላይ የህዝባችን አንድነት ችግሮችን ለማለፍ ትልቅ መሣሪያ ነው ብለዋል ።

የብሔራዊ መረጃ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በበኩላቸው፥ ሰላም ለማምጣት በመጀመሪያ መነጋገርና መግባባት ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን አለፍ ሲልም አጥፊዎችን በህግ መጠየቅ ያስፈልጋል ብለዋል ።

ሰላም ለማስፈን ጠንካራ መዋቅራዊ አደረጃጀት እና የህዝብ የነቃ ተሳትፎ ይጠይቃል ያሉት ደግሞ የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሐም በላይ ናቸው ።

ዶ/ር አብርሐም አክለውም፥ አስተማማኝ ያለው ሰላም ለማረጋገጥ የሰላም ጠንቅ የሆኑ ጉዳዮችን ማጥራት ያስፈልጋል ብለዋል ።

በምክክር መድረኩ ላይ የሰላም ሚኒስቴር ፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር የሰላምና የፀጥታ ተቋማት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የቀጣይ አቅጣጫዎች እንደተቀመጡ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.