አቶ ደመቀ ከሩስያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚካኤል ቦግዳኖቭ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሩስያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚካኤል ቦግዳኖቭ ጋር ተወያይተዋል።
ሚኒስተሮቹ ከ35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ባካሄዱት ውይይት÷የሁለቱን ሀገራት ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
በተለይም በኢነርጂ፣ መሰረተ ልማት፣ ግብርና፣ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ላይ በአገራቱ ትብብር ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚከናወኑፕሮጀክቶችም ተወያይተዋል።
የጋራ ጥቅምን በሚመለከቱ ዋና ዋና ዓለም አቀፍ ሁነቶች ዙሪያም መወያየታቸውንም በኢትዮጵያ ከሩስያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡