Fana: At a Speed of Life!

“ግሎባል ቴሌቪዥን ኔትዎርክ ኦፍ አፍሪካ” የቴሌቪዥን ድርጅት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 5 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ በሊዝ ተረከበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካን ማዕከል አድርጎ የተመሠረተው ግሎባል ቴሌቪዥን ኔትዎርክ ኦፍ አፍሪካ (ጂ ቲ ኤን ኤ) የቴሌቪዥን ድርጅት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 5 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ በሊዝ መረከቡን አስታወቀ፡፡

 

ግሎባል ቴሌቪዥን ኔትዎርክ ኦፍ አፍሪካ (ጂ ቲ ኤን ኤ) ቦታውን ከአዲስ አበባ  ከተማ  አስተዳደር በሊዝ የተረከበው ለጣቢያው ዋና  መስሪያ ቤት ግንባታ ነው፡፡

 

የጣቢያው መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ ግሩም ጫላ በሰጠው መግለጫ÷ የአፍሪካ ድምፅ መሆን የሚችል ዘመናዊ የቴሌቪዥን ተቋም እንደሚገነባ አስረድቷል፡፡

 

የአፍሪካን ገጽታ በመገንባት በዓለም አቀፉ የፖለቲካና የኢኮኖሚ መድረክ አህጉሪቱ ትክክለኛ ቦታዋን እንድታገኝ ለማስቻል መመስረቱን ዋና ስራ አስፈሚው መናገሩን ከኢቢሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.