Fana: At a Speed of Life!

ክፍለ ከተማው በጦርነት ለተጎዱ ወገኖች በአንድ ጀምበር ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ባለሀብቶችን፣ አርሶ አደሮች እና የሃይማኖት አባቶችን በማስተባበር በጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሚውል በአንድ ጀምበር ከ11 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
በመርሃ ግብሩ፥ የአዲስ አበባ የኢንቨስትመንት ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ግርማ ሰይፉ፣ የለሚኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መላኬ አለማየሁ፣ የጊፍት ሪፍት ሪልእስቴት ባለቤት አቶ ገብረኢየሱስ ጋኢታ እንዲሁም የሃይማኖት አባቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
የጊፍት ሪል እስቴት እና አያት ሪል እስቴት እያንዳንዳቸው 3 ሚሊየን፣ የኖህ ሪል እስቴት ደግሞ 1 ሚሊየን ለመስጠት ቃል ገብተዋል፡፡ በተመሳሳይ ሌሎች ባለሀብቶችና የሃይማኖት አባቶች ደግሞ የቀረውን ገንዘብ ለመስጠት ቃል የገቡ ሲሆን፥ በድምሩ ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ቃል መገባቱን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መላኬ አለማየሁ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው፥ ገቢ የማሰባሰብ ስራው ወገኖቻችን እስከ ሚቋቋሙና ወደ ተስተካከለ ህይወታቸው እስከሚመለሱ ድረስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.