Fana: At a Speed of Life!

በቦረና ዞን ለተቅማጥ በሽታ የሚጋለጡ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል – የዞኑ ጤና መምሪያ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ማኅበረሰቡ ለመጠጥ የሚጠቀመው ውሃ ቆሻሻ በመሆኑ ለአደገኛ ተቅማጥ በሽታ መዳረጉን የቦረና ዞን ጤና መምሪያ ገልጿል፡፡

ጤና መምሪያው ÷ ድርቁ በዞኑ ከተከሰተ በኋላ ከፍተኛ የሆነ የውሃ እጥረት አጋጥሟል፣ በዚህም ማኅበረሰቡ ያልታከመ ውሃ ለመጠቀም ተገዷል ሲል ገልጿል፡፡

በዚህም ምክንያት ለተቅማጥ በሽታ የሚጋለጠው ሰው ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ነው የጠቆመው፡፡

የዞኑ ጤና መምርያ ምክትል ሃላፊ ሞሉ ዲማ ÷ በሽታውን ለመከላከል ፣ ውሃውን ለማከም ጥረት እየተደረገ ቢሆንም የማከሚያ ኬሚካሉ በበቂ ሁኔታ እየተገኘ አይደለም ብለዋል፡፡

በዚህ በሽታ የተጠቁትን የማከም ሥራ ቢከወንም በድርቁ ምክንያት ቀያቸውን እየለቀቁ የሚሰደዱ በርካቶች በመሆናቸው ሕክምናውን በተገቢው ማዳረስ አልተቻለም፡፡

ከበሽታው ጋር በተያያዘ ለኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት እና ለኦሮሚያ ጤና ቢሮ በየሣምንቱ ሪፖርት እንደሚደረግና የድንገተኛ መድሐኒቶች እና የውሃ ማከምያ ኬሚካሎች እየተላኩ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ይሁን ና የውሃ ማከሚያ ኬሚካል በበቂ ሁኔታ እየቀረበ አይደለም ብለዋል፡፡

አያይዘውም የድንገተኛ ሕክምና መድሃኒቶች በቂ ባይሆኑም በአቅርቦት የተሻለ የሚባል ደረጃ ላይ እንገኛለን ነው ያሉት፡፡

አቶ ሞሉ ዲማ ÷ የድርቁ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ በተቅማጥ በሽታ የሚታመመው ሰው ቁጥር ከፍተኛ ይሆናል ሲሉ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል፡፡

የዞኑ የውሃ ሽፋን 53 በመቶ የነበረ ሲሆን በድርቁ ምክንያት ወደ 28 ነጥብ 8 በመቶ ወርዷል፡፡

በታሪኩ ለገሰና አፈወርቅ እያዩ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.