Fana: At a Speed of Life!

ቻይና፥ሩሲያና ዩክሬን ግጭትን ከሚያባብስ ድርጊት ታቅበው ውጥረቱን እንዲያረግቡ አሳሰበች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና፥ ሩሲያና ዩክሬን ግጭትን ከሚያባብስ ድርጊት ታቅበው ውጥረቱን እንዲያረግቡ ጥሪ አቀረበች።
 
ቻይና ባወጣችው መግለጫ በዩክሬን ጉዳይ የሚሳተፉ አካላት በሙሉ ከአባባሽ ድርጊት እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርባለች።
 
ቀደም ሲል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቻይና ቋሚ ተወካይ ዣንግ ጁን በተመድ 76ኛው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደተናገሩ፥አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ራሳቸውን በመቆጣጠር ውጥረቱን የሚያባብሱ እርምጃዎችን ከመውሰድ መቆጠብ አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል።
 
በሌላ በኩል ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማቋረጧን አስታውቃለች።
የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ከሰዓታት በፊት በሰጡት መግለጫ ሀገራቸው ከሩሲያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማቋረጧን ማስታወቃቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.