የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን የድንጋይ ከሰል ፍጆታ ለመሸፈን የሚያግዝ የፋብሪካ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን የድንጋይ ከሰል ፍጆታ በሀገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን የሚያግዝ የፋብሪካ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን ታርጫ ዙሪያ ወረዳ ሊገነባ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ እና ማበልፀጊያ ፋብሪካ የጥራት ደረጃው ከፍ ያለ ምርት እዚሁ ከሀገር ቤት ለማግኘት እንደሚያግዝ ተገልጿል።
ፋብሪካው በኢስት አፍሪካን የማእድን ኮርፖሬሽን ተገንበቶ ወደ ስራ እንደሚገባም ነው የተነገረው።
በፋብሪካ ግንባታ ማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ነጋሽ ዋጌሾ፣ የኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ ኩባንያ ባለቤት አቶ ብዟየሁ ታደለ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለሰልጣናት ተገኝተዋል።
የድንጋይ ከሰል ማምረቻ ፕሮጀክቶቹ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ አጠቃላይ ካፒታል ያላቸውና በምስራቅ አፍሪካ ሆልዲንግስ እና በኢቲ የማዕድን ልማት አክሲዮን ማህበር የሚገነቡ መሆቸውን ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገልጸዋል፡፡
ፕሮጀክቶቹ በአመት ከ700 ሺህ ቶን በላይ የድንጋይ ከሰል የሚያመርቱ ሲሆን÷ ይህም በአጭር ጊዜ ውስጥ የድንጋይ ከሰል ምርትን በሀገር ውስጥ ለመተካት የምናደርገውን ጥረት በከፍተኛ መጠን የሚደግፍ ይሆናልም ነው ያሉት፡፡
የድንጋይ ከሰል ምርት ስራው የሁለት መቶ ሚሊየን ብር ኢንቨስትመንት ሲሆን÷ ለ200 ሰዎች የስራ ዕድል ይፈጥራልም ተብሏል።
በበርናባስ ተስፋዬ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!