ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ አበባ የከተማ ግብርና ስራዎች ያለበትን ሁኔታ ተመለከቱ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክ/ከተሞች በመዘዋወር የከተማ ግብርና ስራዎች ያለበትን ሁኔታ ተመልክተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የከተማ ግብርና እንቅስቃሴዎች ለሀገር አቀፍ የምግብ ዋስትና እንቅስቃሴዎች ትልቅ ፋይዳ እንዳላቸው በተደጋጋሚ መግለፃቸው የሚታወቅ ሲሆን ÷ዛሬም በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ የቤተሰብና የአካባቢ የከተማ ግብርና እንቅስቃሴዎች ያሉበትን ደረጃ ተዘዋውረው መመልከታቸውን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡