Fana: At a Speed of Life!

የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር እና የጉሙዝ ብሄረሰብ ምክር ቤቶች ውይይት እያካሄዱ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ምክር ቤትና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የጉሙዝ ብሔረሰብ ምክር ቤት በመተከል ዞን አጎራባች የወረዳ ምክር ቤቶች የጋራ ውይይት በግልገል በለስ ከተማ እያካሄዱ ነው።
 
በውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት “የጉምዝ ብሔረሰብ አፈ-ጉባዔ አቶ ጆንሴ ኢብሳ ህዝቡ አንድ ነው፣ ወደ ነበረበት ሰላሙና አንድነቱ እንዲመለስ አመራሩ ከልቡ መመለስና አንድ መሆን አለበት”ብለዋል።
በመድረኩ የሁለቱ ክልል አጎራባች ወረዳዎች ህዝብ የቀደመ ሰላሙ ተመልሶ በሰላም በሚኖርበት ሁኔታ ላይ ይመከርበታል።
 
በሁለቱ ዞኖች መካከል የሰላምና የልማት የመግባቢያ ሰነድ የመፈራረም ስነ ስርዓት ይካሄዳል ተብሎ እንደሚጠበቅም ከአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.