በደባርቅ ከተማ ለህብረተሰቡ በእርዳታ መልክ የተሰራጨ 111 ኩንታል የአተር ክክ በሕገወጥ ነጋዴዎች ተሰብስቦ ከከተማዋ ሊወጣ ሲል ተያዘ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደባርቅ ከተማ ለህብረተሰቡ በእርዳታ መልክ የተሰራጨ 111 ኩንታል የአተር ክክ በሕገወጥ ነጋዴዎች ተሰብስቦ ከከተማዋ ሊወጣ ሲል መያዙን የከተማዋ ንግድ ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አዲሱ እንደገለጹት÷ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በተሰራው ሥራ በእርዳታ መልክ ለሕብረተሰቡ ተሰራጭቶ የነበረ ነገር ግን በህገወጥ ነጋዴዎች የተያዘ 111 ኩንታል ክክ በሕገወጥ መንገድ ከደባርቅ ወደ ጎንደር ሊወጣ ሲል ሊያዝ ችሏል፡፡
የተያዘውን ክክ በንግድ ግብረ ሀይል ተወስኖ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማህበረሰቡ ለገበያ ይቀርባል መባሉን ከደባርቅ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!