በጅቡቲ ‘ፒፕልስ ራሊ ፎር ፕሮግረስ’ ፓርቲ ዋና ፀሐፊና የሀገሪቱ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ኢልያስ ሙሳ ዳዋሌህ የተመራ ልዑክ በብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገባ
የጅቡቲ ‘ፒፕልስ ራሊ ፎር ፕሮግረስ’ ፓርቲ ዋና ፀሐፊና የሀገሪቱ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ኢልያስ ሙሳ ዳዋሌህ የተመራ ልዑክ ከነገ ጀምሮ በሚካሄደው የብልፅግና ፓርቲ 1ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ለመታደም አዲስ አበባ ገብቷል።
ከዋና ፀሐፊው ጋር የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የሀገሪቱ የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ አብዲ ፋራህ እና የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አህመድ ዲኒ አሌኦ በጉባኤው ለመታደም መጥተዋል።
እንግዶቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትርና የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ አህመድ ሺዴ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ጌንባታ ማዕከል አስተባባሪ አምባሳደር ሐሰን አብዱልቃድር በርከት እንዲሁም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል አምባሳደር ፍስሐ ሻውል አቀባበል እንዳደረጉላቸው ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል።
የጅቡቲ ‘ፒፕልስ ራሊ ፎር ፕሮግረስ’ ፓርቲ ልዑካን የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።