Fana: At a Speed of Life!

የብልፅግና ፓርቲ ከኢትዮጵያ አልፎ ለቀጠናው እድገት ተስፋን የሰነቀ ነው-የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲ ከኢትዮጵያ አልፎ ለቀጠናው እድገት ተስፋን የሰነቀ ነው ሲሉ የደቡብ አፍሪካው ገዥ ፓርቲ የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ፕሮፌሰር ኢክባል ጃዝብሃይ ተናገሩ፡፡
 
ፕሮፌሰሩ በብልፅግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ የብልጽግና ፕሬዚዳንትና የኤፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ሰላም እንዲፈጠር ያደረጉትን ጥረት እና ያስመዘገቡትን የሰላም ውጤት አድንቀዋል፡፡
 
በተጨማሪም ከኢትዮጵያ ሚኒስትሮች 50 በመቶው ሴቶች መሆናቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሴቶችን ተሳትፎና የመወሰን ስልጣን ለማሳደግ በቁርጠኝነት እየሰሩ መሆናቸው ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
 
የአፍሪካ ትልቁ ፕሮጀክት የሆነው የዓባይ ግድብ ኃይል ማመንጨት መጀመሩም ሀገሪቱ በእድገት ጎዳና ላይ መሆኗን አመላካች መሆኑን ገልጸዋል፡፡
 
በኢትዮጵያ የተጀመረው የበቃ ወይም No More እንቅስቃሴ በ27 የዓለም ከተሞች ተቀባይነትን በማግኘቱ አፍሪካውያን ኢምፔሪያሊስቶች የሚያደርሱትን ጫና በመቃወም ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
 
ፓርቲያቸው የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ ከብልፅግና ፓርቲ ጋር በተለያዩ ዘርፎች በትብብር ይሰራል ያሉት ፕሮፌሰር ኢክባል ጃዝብሃይ፥ ብልፅግና ፓርቲ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ለቀጠናው ብሎም ለአፍሪካ ተስፋን የሰነቀ ፓርቲ ነው ብለዋል፡፡
 
በሚኪያስ ዓየለ
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.