Fana: At a Speed of Life!

የቲቢ ምርመራ ዘመቻ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መጋቢት 15 ቀን የሚከበረውን የዓለም የቲቢ ቀን ምክንያት በማድረግ የቲቢ ምርመራ ዘመቻ ተጀመረ።

ሪች ኢትዮጵያ በተሰኘ ድርጅት አስተባባሪነት ለቲቢ በሽታ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የቲቪ ምርመራ ይካሄዳል ተብሏል።

ዛሬም በማረሚያ ቤቶች ያለው የቲቢ ስርጭት ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለሚገኙ ታራሚዎች የቲቢ በሽታ ምርመራ እና ልየታ ተጀምሯል።

ሪች ኢትዮጵያ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ እና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በመተባባር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ40ኛ ጊዜ በሃገር አቀፍ ደግሞ ለ25ኛ ጊዜ ”ቲቢን ለማጥፋት የድርሻችን እናበርክት፤ ህይወት እንታደግ” በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የቲቢ ቀን በደማቁ ለማክበር እና ስለ በሽታው ይበልጥ ግንዛቤ እንዲኖር በማድረግ ለማክበር እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

በኢትዮጵያ በ2013 ዓ.ም 151 ሺህ ሰዎች በቲቢ በሽታ እንደታመሙ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች በቲቢ በሽታ ህይወታቸው እንደሚያልፍ ጥናቶች ያመላክታሉ።

በምንይችል አዘዘው

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.