Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያው ፕሬዚዳንት እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር የሩሲያ እና ዩክሬን ቀውስን አስመልክተው ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት ጋር የሩሲያን እና የዩክሬንን ቀውስ በሰላማዊ መንገድ መፍታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በስልክ ተወያዩ።

ፕሬዜዳንት ፑቲን በሩሲያ እና በዩክሬን ተወካዮች መካከል በቪዲዮ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ስላለው ድርድር ለእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኔት ማብራሪያ ሰጥተዋቸዋል።

የእስራኤሉ ጠቅላ ሚኒስትር ቤኔት በበኩላቸው ÷ የሩስያ እና የዩክሬንን ቀውስ በሚመለከት ከበርካታ ሀገራት መሪዎች ጋር ስላደረጉት ውይይት ለፑቲን ገለጻ አድርገውላቸዋል ።

ሁለቱ መሪዎች በዶንባስ የሚገኙትን ሪፐብሊኮች ለመከላከል በሚደረገው ልዩ ዘመቻ የሀሳብ ልውውጥ ማድረግ መቀጠላቸውንም ዘገባው ጠቁሟል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ÷ፕሬዜዳንት ፑቲን በዛሬው እለት በዶኔትስክ ማዕከላዊ ክፍል ዩክሬን ያደረሰችው የሚሳኤል ጥቃት በርካታ ንጹሃን ላይ ጉዳት ያደረሰ አረመኒያዊ ድርጊት ነው ሲሉ ኮንነውታል፡፡

ለ20 ቀናት የቀጠለው የሩስያ እና የዩክሬን ቀውስ ዓለም አቀፍ ውግዘትን ያስከተለ ሲሆን፥ በሞስኮ ላይም የገንዘብ ማዕቀብ እንዲጣል እና ዓለም አቀፍ ኩባንያዎችም ከሀገቱ እንዲወጡ ማድረጉን ዘገባው አስታውሷል፡፡

ጦርነቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በዩክሬን ቢያንስ 636 ንፁሃን ዜጎች ሲገደሉ 1ሺህ 125 ቆስለዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው መረጃ አሳውቋል፡፡

ወደ 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ወደ ጎረቤት ሀገራት መሰደዳቸውንም የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ አስታውቋል ሲል አናዶሉ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.